ካንሰርን በመጀመሪያ ደረጃ በሚባለው የስርጭት ሂደት ላይ እያለ ወደ ህክምና በመሄድ መከላከል እንችላለን

ካንሰርን በመጀመሪያ ደረጃ በሚባለው የስርጭት ሂደት ላይ እያለ ወደ ህክምና በመሄድ መከላከል እንችላለን እንዲሁም የ ካንሰር ስሜቶች ናቸው ብለን ካሰብን ቶሎ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ እና ክትትላችን ባለማቆም፣ ቀድመን ከባለሙያ ግንዛቤ በመውሰድ ቅድመ መከላከል በማድረግ ካንሰርን በቀላሉ ማሸነፍ እንችላለን ። እኛም በተለያዩ ተቋማት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን እየሰጠን እንገኛለን። አዲስ አበባ በሚገኙ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለ11 እና 12 ተኛ ክፍል ተማሪዎች ፣በአየር ጤና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ፣ በየማነ ብርሃን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፣በካቶሊክ ካቴድራል ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እና በ ቀራኒዮ መድሃኒአለም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለሴት ተማሪዎች ስለ ጡት ካንሰር እና የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ስልጠናዎችን ሰተናል። አሁንም ስልጠናው በተለያዩ ተቋማት ይቀጥላል። እናቶች እና ሴት እህቶችን ከአስከፊው ካንሰር በሽታ እንታደግ። “አለምፀሀይ የጡት ካንሰር ፋውንዴሽን”
telegram:>https://t.me/abcfpinkhouse
website፡> www.abcfonline.org

Spread the love

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *