የጡት ካንሰር ግንዛቤ ኮንፈረንስ መርሀ ግብ ተካሄደ

የጡት ካንሰር ግንዛቤ ኮንፈረንስ መርሀ ግብ ተካሄደ

****

(አዲስ አባ ህዳር 25/2016 ዓ.ም) ኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በክብር እንግድነት በተገኙበት የጡት ካንሰር ግንዛቤ ኮንፈረንስ መርሀ ግብ ተካሄደ።

በመክፈቻ ስነስርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ሚኒስትሯ ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ይህ የዓመታዊ የጡት ካንሰር ግንዛቤ ኮንፈረንስ ስለበሽታው ግ

ንዛቤ ለመፍጠር፣ ተጨማሪ እርምጃዎችን ለመውሰድ እና የጡት ካንሰር በሴቶች ላይ የሚያደርሰውን ተፅእኖ ለመቀነስ ምቹ አጋጣሚ ነው በማለት ለሁነቱ ክንውን ክብርት የአለምፍሬ ፒንክ ሀውስ የካንሰር ፋውንዴሽን መስራች እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዶክተር ፍሬህይወት ድርሶን አመስግነዋል።

ክብርት ሚኒስትሯ አክለውም የጡት ካንሰር በሴቶች ላይ ከሚከሰቱት የካንሰር ዓይነቶች ግንባር ቀደም የካንሰር አይነት እንደሆነና የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያመለክተው በ2020GC፣ 2.3 ሚሊዮን ሴቶች በጡት ካንሰር የተያዙ ሲሆን 685,000 ሴቶች ደግሞ በአለም አቀፍ ደረጃ ለሞት ተዳርገዋል ብለዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያ በየአመቱ ከ15,000 በላይ ሴቶች በጡት ካንሰር እንደሚሞቱ ጥናቶች ያሳያሉ። ይህ የችግሩን ስፋት እና ጥልቀት በግልፅ የሚያሳይ በተለያዩ ምክንያቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ፣ የካንሰር ቅድመ ምርመራ እና የጤና ስርዓት ተግዳሮትና የጥራት ችግር ጋር ተደምሮ በታዳጊ ሀገራት ያሉ ሴቶች የሞት መጠን ከፍ ያደርገዋል በማለት በመግለፅ ለዚህም የመፍትሄ እርምጃ ለመውሰድ የሚገባን ወሳኝ ተግባር ነው በሽታው በደንብ ሳይሰራጭና በቀላሉ ውጤታማ ህክምና ለማድረግ ሴቶች የጡት ካንሰር ምልክቶች አስቀድሞ በመረዳት እና በየጊዜው ራስን በመመርመር ያለውን ጥቅም ማወቅ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የመጀመርያ ደረጃ የጤና አገልግሎትን ተደራሽነት በመላ ሀገሪቱ ለማስፋፋት ደረጃ በደረጃ ዕርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑንም አክለው ገልፀዋል።

የአለምፍሬ ፋውንዴሽን ድርጅት ኃላፊና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች መርሃ ግብሩን አስመልክቶ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።

Spread the love

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *