ለካንሰር ታማሚዎች የድጋፍ ጥሪ ቀረበ

ለካንሰር ታማሚዎች የድጋፍ ጥሪ ቀረበ
*************
(ኢፕድ)

የዓለምፍሬ ፒንክ ሃውስ ካንሰር ፋውንዴሽን ህብረተሰቡ ለካንሰር ታማሚያን የሚውል ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረበ።

የፋውንዴሽኑ መስራችና የቦርድ አባል ወይዘሮ ፀዳለፅጌ አላዩ እንደገለፁት፤ ፋውንዴሽኑ ለ13 ዓመታት በካንሰር ህመም ላይ ቅድመ መከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫ ከመስጠት ጀምሮ ለካንሰር ታካሚዎች የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ ቆይቷል።

በዚህም በአዲስ አበባ እና በጎንደር ከተማ ከስምንት ሺህ በላይ የካንስር ታማሚዎችን የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ አድርጓል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ለታማሚዎች የምግብ፣ መጠለያ፣ ትራንስፖርት እና መድኃኒት መግዣ የመሳሰሉ እርዳታዎችን ሰጥቷል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ፋውንዴሽኑ ምንም አይነት ቋሚ ገቢ የሌለውና ድርጅቶች ጋር እየሰራ እንዳልሆነ ጠቅሰው፤ ይህም የተቋቋመበትን አላማ ለማሳካት ተግዳሮት የሆነበት መሆኑን አንስተዋል።

በመሆኑም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገራት የሚነኙ በጎ ፍቃደኞች የገንዘብ እና የአይነት ድጋፎችን በአዲስ አበባ የካ ጤና ጣቢያ በሚገኘው የፋውንዴሽኑ አድራሻ እንዲለግሱ ጥሪ አቅርበዋል።

የፋውንዴሽኑ የበጎፍቃድ አምባሳደር ጋዜጠኛ እስክንድር ላቀው በበኩሉ፤ የበሽታው የህክምና ወጪ፣ ትራንስፖርትና መጠለያ ማግኘት በተለይም ከሩቅ አካባቢ በሚመጡ ታካሚዎች ላይ ተጨማሪ ጫና የሚፈጥር መሆኑን በመረዳት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

በማህሌት ብዙነህ

Spread the love

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *