አለም ፍሬ ፒንክ ሃውስ ካንሰር ፋውዴሽን ለአራተኛ ጊዜ የማህፀን በር ጫፍ እና የጡት የካንሰር የግንዛቤ ማስጨበጫ ብርታትሽ ብርታቴ በሚል መሪ ቃል የአምስት ኪሎሜትር የእግር ጉዞ መነሻውን በመስቀል አደባባይ በማድረግ በቴድሮስ አደባባይ መጨረሻውን በጊዮን ሆቴል አርጓል
በዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ላይ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በመገኘት የግንዛቤ መስጫ ፕሮግራሙን አስጀምረዋል
በማስጀመሪያው ስነስርአት ላይ የጤና ሚንስትራ ዶክተር መቅደስ የጤና ሚኒስቴር በመከላከል ያተኮረ ስራ እየሰራ ቢሆንም ካንሰርን ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራ አደሚገኝ እና የካንሰር ቅድመ ምርመራ እና ህመሙ ቶሎ ከታወቀ ማከም ማዳን በሚል መርህ እደ ሃገር እየሰራ ይገኛል ብለዋል
የሴቶች እና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ በበኩላቸው ከተለያዩ ክልሎች መጥተው ህክምናቸውን በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለሚከታተሉ እናቶች እና እህቶች አቅም ለሌላችው ድጋፍ ለሚያረገው አለምፍሬ ፒንክ ሃውስ ጋር በጋራ ለመስራት እና የበኩላቸውን ድረሻ ለመወጣት ቃል ገብተዋል
አለም ፍሬፒነንክ ሃውስ ካንሰር ፋውዴሽን መስራች እና ዳይሬክተር ዶክተር ፍሬህይወት ደርሶ በአዲሰስ አበባና በጎንደር አቅም እና ረዳት ለሌላችው እናቶች እና እህቶች የምግብ የመጠለያ የንፅህና መጠበቂያ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠ አደሚገኝ ገልፀው ይህ ስራ የሁሉም ርብርብ እደሚያስፈልገው ገልፀው ፕሮግራሙ ተጠናቋል













